እኔ መሞት ካለብኝ

Translated to Amharic by

እኔ መሞት ካለብኝ

አናንተ መኖር አለባችሁ

ታሪኬን እንድትነግሩልኝ

እቃዬን አንድትሸጡልኝ

አንድ ቁራጭ ጨርቅ ገታችሁ

እና ጥቂት ክሮች

(ረጅም አድርጉት ፣ መልኩ ድግሞ ነጭ)

አንድ ልጅ በጋዛ የሆነ ቦታ

መንግስተ ሰማይን ቀና ብሎ ሲይይ

በአንድ ብልጭታ

ምንንም ሳይሰናብት-

የገዛ ልጆቹን እንኳዋን

እራሱን ራሱ ሳይሰናበት-

የሄድው አባቱን ሲጠባበቅ

እናንተ የሰራችሁት ወላንዶ

ለእኔ የሰራችሁት ወላንዶ

ከፍ ብሎ ሲበር አይቶ

ፍቅርን ይዞ ሊመለስ

የሄደ መልአክ ነው

ብሎ እንዲያስብ

እኔ መሞትካለብኝ

ሞቴ ተስፋ ይዞ ያምጣ

ሞቴ ይሁን ታሪክ።


A poem by Refaat Alareer.